Home
ጎበና: ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1810-1881): [Gobena: A Military and Political Life (1810-1881)]
Loading Inventory...
Barnes and Noble
ጎበና: ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1810-1881): [Gobena: A Military and Political Life (1810-1881)]
Current price: $49.95
Barnes and Noble
ጎበና: ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሕይወት (1810-1881): [Gobena: A Military and Political Life (1810-1881)]
Current price: $49.95
Loading Inventory...
Size: Hardcover
*Product Information may vary - to confirm product availability, pricing, and additional information please contact Barnes and Noble
ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ታላቅ ሚና ስለተጫወቱት የፖለቲካ ሰውና የጦር መሪ የራስ ጎበና ዳጪን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ነው።
በአራት ክፍሎችና በዓሥራ አራት ምዕራፎች ተዋቅሮ ክፍል አንድ ከዋናው የታሪክ ዳሰሳና ትንተና በፊት ታሪካዊውን ዳራ ለመተረክ ይሞክራል። ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ጎበና ሊደርስ ከቻለበት የወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ የእውቅና ጣርያ ድረስ ያለፈባቸውን በፈተና የተሞሉ፣ የዚያኑ ያክል በውጤት የታጀቡ የሕይወት ልምዶቹን ለመዳሰስ ጥረት የሚያደርግ ሲሆን፤ ሦስተኛው ከዚሁ ተያያዥ በሆነ መልኩ ጎበና የተጎናጸፈውን እውቅና እንደምን አድርጎ ሀገራዊ ፋይዳ ወደአለው ነገር እንደለወጠ ለማሳየት ይጥራል። ክፍል አራት የጎበና የመጨረሻ ዘመናት ያለ አቻ ወራሽ ሲጠናቀቁ የኦሮሞ ሕዝብ የተጋረጠበትን ከሀገርና ከመንግሥት ባለቤትነት የመንሸራተት ፈተና ለምን እንደተከሠተ ለማመላከት ጥረት ያደርጋል።
በዝርዝር ምዕራፎቹ ስለ ጎበና እስከ አሁን የነበሩትን የተለያዩ እይታዎችና አመለካከቶች፣ ከጎበና መወለድ በፊት በዓሥራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን መጀመሪያና በልደቱ ወቅት የጎበና የትውልድ ቦታ በነበረው ሰሜን ሸዋ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ በይበልጥ ደግሞ የኦሮሞና ዐማራ ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ጎበናን እንዴት እንደቀረጹት፣ የጎበናን ልደት፣ ልጅነትና ወጣትነት እንዲሁም የሎሌነት፣ የአማችነት እና ደጅ አጋፋሪነት በመጨረሻም የሽፍትነት ጊዜውን፣ የግዛት መስፋፋትና የሰፊውን ኢትዮጵያ ሀገር የመመሠረት ውጥንና ከምኒልክ ጋር መተዋወቁን ይገልጻል።
ጎበና የተለያዩ ሹመቶችን ለምሣሌ የደጃዝማችነትና ከዚያም የራስነት ሹመትና ማዕረግ ላይ እንዴት እንደደረሰና በተለይም የጦር አበጋዝነትን ያክል ትልቅ ሃላፊነት አንዴት እንደወሰደ በተጓዳኝም "የግዛት ማስፋፋትና ሀገር ማቅናት" ስተራቴጂ እንዴት በጋራ እንደተነደፈ፣ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተለያዩ መሪዎች እንደተተገበረ ይተርካል። በመጨረሻም ጎበና ብዙዎቹን የቤት ሥራዎቹን ቀድሞ በማጠናቀቁና ሌሎቹን ባለድርሻ አካላት ድንክዬ በማድረጉ በምኒልክ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ጉትጎታና ማጉረምረም በመጀመሪያው ስምምነት መሠረት ሳይሆን ውጤቱን በማጠፍ ጎበና ያስገበራቸውን አካባቢዎች ሌሎች እንደ ተሾሙበት፣ የጎበናን ሃይማኖታዊ ክንውንና የአብያተክርስቲያናት ግንባታ እንቅስቃሴ እንዱሁም ቤተሰባዊ ሕይወቱን በተለይም ጋብቻና ልጆች፣ ሞትና አሟሟቱን በተመለከተ ማስረጃ እስከፈቀደ ድረስ ተገልጾ በመዝጊያውም ስለጎበና የተነገረው ነገር ያለውን አንድምታ በጸሐፊው ግንዛቤ ልክ የማሰሪያ ሐሳብ የተሰጠበት መጽሐፍ ነው።